Database CH-2, Database Concepts, Organization Study to design database, Schemes and Mind Maps of Information Systems

Database CH-2, Database Concepts, Organization Study to design database

Typology: Schemes and Mind Maps

2020/2021

Uploaded on 09/05/2023

ileadeth-after7yrs
ileadeth-after7yrs 🇪🇹

3 documents

1 / 66

Toggle sidebar

This page cannot be seen from the preview

Don't miss anything!

bg1
መጋቢት/2010 ዓ.ም
ገ/ኢ/ት/ሚ/ር
የፋይናንስ የህግ
ማዕቀፍ
ፕሮግራም
በጀት
ፊስካል
ፖሊሲ
ኤሌክትሮኒክ
ግዥ
ኤሌክትሮኒክ
ክፍያ
ዘመናዊ ሂሳብ
አያያዝና ሪፖርት
ዘመናዊ ንብረት
አስተዳደር
የውስጥ
ቁጥጥር ስርዓት
የፋይናንስ ዘመናዊ
ቴክኖሎጂ
የአቅም ግንባታ
ፋይናንስ
ግልፅነትና
ተጣቂነት
ማህበራዊ
ተጠያቂት
የመንግስት ፋይናንስ
አስተዳደር ስትራቴጂክ ዕቅድ
(2010-2014)
pf3
pf4
pf5
pf8
pf9
pfa
pfd
pfe
pff
pf12
pf13
pf14
pf15
pf16
pf17
pf18
pf19
pf1a
pf1b
pf1c
pf1d
pf1e
pf1f
pf20
pf21
pf22
pf23
pf24
pf25
pf26
pf27
pf28
pf29
pf2a
pf2b
pf2c
pf2d
pf2e
pf2f
pf30
pf31
pf32
pf33
pf34
pf35
pf36
pf37
pf38
pf39
pf3a
pf3b
pf3c
pf3d
pf3e
pf3f
pf40
pf41
pf42

Partial preview of the text

Download Database CH-2, Database Concepts, Organization Study to design database and more Schemes and Mind Maps Information Systems in PDF only on Docsity!

መጋቢት/2010 ዓ.ም ገ/ኢ/ት/ሚ/ር

የፋይናንስ የህግ ማዕቀፍ ፕሮግራም በጀት

ፊስካል ፖሊሲ

ኤሌክትሮኒክ ግዥ

ኤሌክትሮኒክ ክፍያ

ዘመናዊ ሂሳብ አያያዝና ሪፖርት ዘመናዊ ንብረት አስተዳደር

የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት

የፋይናንስ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ

የአቅም ግንባታ

ፋይናንስ ግልፅነትና ተጣቂነት

ማህበራዊ ተጠያቂት

መጋቢት/2010 ዓ.ም ገ/ኢ/ት/ሚ/ር

የፋይናንስ የህግ ማዕቀፍ ፕሮግራም በጀት

ፊስካል ፖሊሲ

ኤሌክትሮኒክ ግዥ

ኤሌክትሮኒክ ክፍያ

ዘመናዊ ሂሳብ አያያዝና ሪፖርት ዘመናዊ ንብረት አስተዳደር

የውስጥ ቁጥጥር ስርዓት

የፋይናንስ ዘመናዊ ቴክኖሎጂ

የአቅም ግንባታ

ፋይናንስ ግልፅነትና ተጣቂነት

ማህበራዊ ተጠያቂት

    1. መግቢያ
    • 1.1 የትኩረት አቅጣጫዎች
    • 1.1.1 ራዕይ (Vision) - ሀ. የሚኒስቴሩ ራዕይ - ለ. የስትራቴጂው ራዕይ
      • 1.1.2 ተልዕኮ (Mission) - ሀ. የሚኒስቴሩ ተልዕኮ - ለ. የስትራቴጂው ተልዕኮ
      • 1.2 የስትራቴጂው ዓላማ
        • 1.2.1. የስትራቴጂው ዋና ዓላማ
        • 1.2.2. የስትራቴጂው ዝርዝር ዓላማዎች
      • 1.3 የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ትርጓሜ
      • 1.4 የስትራቴጂው ወሰን
    1. የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር የማሻሻያ ስራዎች አጀማመር
    1. የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ማሻሻያ ስራዎችና የተገኙ ውጤቶች
    • 3.1. የሕግ ማዕቀፍ
    • 3.2. የመካከለኛ ዘመን ፊሲካል ማዕቀፍ እና የፕሮግራም በጀት
    • 3.2.1. የመንግሥት ገቢ እና ወጪ ዕቅድ ማሻሻያ
    • 3.2.2. የመንግስት በጀት ዝግጅትና አስተዳደር
    • 3.3. የመንግሥት ጥሬ ገንዘብ፣ ክፍያ እና ብድር አስተዳደር ሥርዓት
    • 3.3.1. የመንግሥት ጥሬ ገንዘብ አስተዳደር እና ክፍያ ሥርዓት
    • 3.3.2. የመንግሥት ብድር አስተዳደር ሥርዓት
    • 3.4. የመንግስት የሂሳብ አያያዝና ሪፖርት አቀራረብ ሥርዓት
    • 3.5. የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር
    • 3.6. የውስጥ ኦዲት
    • 3.7. ዘመናዊ የመረጃ ስርዓት አጠቃቀም
    • 3.8. የፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት
    1. ልማታዊ መንግስት እና የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር
    • 4.1. የመንግሥት ገቢ ማሻሻያ
    • 4.2. የመንግሥት ወጪ አመዳደብና አስተዳደር
    • 4.3. የልማትና የድህነት ቅነሳ ፖሊሲና እስትራቴጂ
    • 4.4. ድህነት ተኮር ወጪዎች
    • 4.5. የመንግሥት ወጪን ውጤታማ ማድረግ
    • 4.6. ያልተማከለ የፋይናንስ አስተዳደር (DEEPEN FISCAL DECENTRALIZTION)
    1. ውስጣዊ እና ውጫዊ ሁኔታዎች ትንተና
    • 5.1. ውስጣዊ ሁኔታ
    • 5.2. ውጫዊ ሁኔታ ዳሰሳ
    • 5.2.1. መልካም አጋጣሚዎች
    • 5.2.2. ሥጋቶች
    • 5.2.3. አስቻይና ፈታኝ ሁኔታዎች
    1. የስትራቴጂው የትኩረት መስኮችና ግቦች
    1. የስትራቴጅው አመራርና ተቋማዊ አደረጃጀት
    • 7.1. ስትራቴጅውን ለመምራት ዋና ዋና መሰረታዊ ጉዳዮች (MAIN PRINCIPLES)
    • 7.2. ተቋማዊ አደረጃጀት፣ ክትትልና ግምገማ
    • 7.3. ስትራቴጂውን ለማስፈጸም የሚያስፈልግ በጀት
    • 7.4. የስትራቴጂክ ዕቅድ ትግበራ የድርጊት መርሐ ግብር (Result Framework)

“የአገራችንን የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ይበልጥ በማሻሻል በስትራቴጂው ዘመን መጨረሻ ላይ ከአፍሪካ የላቀ የፋይናንስ አስተዳደር ስርዓት መሆን ነው”

1.1.2 ተልዕኮ (Mission)

ሀ. የሚኒስቴሩ ተልዕኮ

  • የተቋም አቅም ግንባታ፣
  • ፊስካል ፖሊሲ፣
  • መንግስት ፋይናንስ አስተዳደር እና
  • የውጪ ሀብት ማሰባሰብና አጋርነት ማጎልበት ለ. የስትራቴጂው ተልዕኮ

“የአገራችንን የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደርን ዘመናዊ፣ ቀልጣፋና ውጤታማ በማድረግ ግልፀኝነትን፣ ተጠያቂነትንና ፍትሃዊነት የሚያሰፍን እና ለኢኮኖሚ ዕድገት አጋዥ እንዲሆን ማድረግ ነው ”

1.2.1. የስትራቴጂው ዋና ዓላማ የስትራቴጂው ዋና ዓላማ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር የአገሪቱን የልማት ስትራቴጂ መሰረት ያደረገ ዘመናዊ፣ ቀልጣፋ፣ተጠያቂነት የሰፈነበትና ውጤታማ እንዲሆን ለማስቻል ነው፡፡

1.2.2. የስትራቴጂው ዝርዝር ዓላማዎች ስትራቴጂው የሚከተሉት ዝርዝር ዓላማዎች አሉት፡-

ሀ) ውጤታማ የሆነና በመከከለኛ ጊዜ የልማት ዕቅድ ላይ የተመሰረተ የፕሮግራም በጀት ስርዓት ለማስፈን፣ ለ) የጥሬ ገንዘብ ክፍያና አስተዳደር ስርዓት ለማሻሻል፣

ሐ) የመንግስት ፋይናንስ ሪፖረት አቀራረብ አለማቀፍ ደረጃውን የጠበቀ እንዲሆን በማድረግ

ጥራቱን የጠበቀ፣ የተሟላና ተጠያቂነትን የሚያሰፍን ለውሳኔ ሰጪው አካል የፋይናንስ መረጃን በማቅረብ የውስጥ ቁጥጥር ስርዓቱን ለማጠናከር፣

መ) የተቀናጀ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር የመረጃ ሥርዓት (IFMIS) የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር የምዝገባ ስርዓት እንዲሆን ለማስቻል፣ ሠ) የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር መረጃዎች ለዜጎች ተደራሽን እንዲሆኑ በማድረግ ግልጽነትን፣ ተጠያቂነትንና አሳታፊነትን ለማስፈን፣

ረ) የመንግስት ግዥና ንብረት አስተዳደር በዘመናዊ ስርዓት እንዲመራ ለማድረግ ፣ ሰ) በመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ተግባራት ላይ የሚሳተፉ ባለሙያዎች የሙያ ደረጃ እና ብቃት ለማሳደግ፣

ሸ) የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር የማሻሻያ ስራዎች ስርዓተ ፆታን እና ልዩ ልዩ ፍላጎት ያላቸውን የማህበረሰብ ክፍሎች አሳታፊነት እና ተጠቃሚነት ማሳደግ፣ ነው፡፡

የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት እና ሃገሮች የተለያየ ትርጓሜ የተሰጠው ሲሆን በዚህ ስትራቴጂ የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ማለት የፊሲካል ፖሊሲን፣ በጀት አስተዳደርን፣ የጥሬ ገንዘብ ክፍያና አስተዳደርን፣ የብድር አስተዳደርን፣ የሂሳብ አያያዝና ሪፖርትን አቀራረብን፣የኦዲትና የውስጥ ቁጥጥርን፣ የግዥና ንብረት አስተዳደርን እና ሌሎች ተያያዥ የክትትል ስራዎች ማለት ነው፡፡

ይህ ስትራቴጂ የሚተገበረው ከ2010 እስከ 2014 በጀት ዓመት ሲሆን የትግበራ መስኮቹ የፊሲካል ፖሊሲ፣ ታክስ ፖሊሲ፣ የፕሮግራም በጀት፣ የጥሬ ገንዘብ ዝግጅትና የክፍያ አስተዳደር፣ የብድር አስተዳደር፣ የመንግስት የሂሳብ አያያዝና ሪፖርት አቀራረብ፣ የውስጥ ኦዲትና ቁጥጥር፣ የግዥ እና ንብረት አስተዳደር፣ የመረጃና የክትትል ስርዓት እና የመንግስትና የግል አጋርነት ያጠቃልላል፡፡

ከ1983 በጀት ዓመት በፊት የአገራችን የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር የተሟላ የሕግ ማዕቀፍ ስላልነበረው ፋይናንሱን በማስተዳደርና በመቆጣጠር በኩል ከፍተኛ ችግሮችና ክፍተቶች ነበሩበት፡፡ በዚህም ምክንያት የተነሳ በ1987 በጀት ዓመት የጠቅላይ ሚኒስቴር ጽ/ቤት ከፍተኛ

  • በመንግሥት የፋይናንስ አስተዳደሩ ከፍተኛ ብቃት ያለው የባለሙያ እጥረት መኖሩ፣ የሂሣብ ባለሙያዎችንና (አካውንታንቶችንና) ኦዲተሮችን የማብቃት የሥልጠና ሥርዓቶች አለመኖራቸው የሚሉት ይገኙበታል፡፡

ከላይ የተዘረዘሩትን የጥናቱን ውጤቶች መሠረት በማድረግ በአገሪቱ የሚገኘውን የሲቪል ሰርቪስ ሚናና አወቃቀር በአዲስ መልክ ማሻሻል ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ሪፎርም ፕሮግራም ከሲቪል ሰርቪስ ሪፎርም አምስቱ ንዑሳን ፕሮግራሞች አንዱ ሆኖ እንዲቀረጽ ተደረጓል፡፡ የመንግሥት ወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ማሻሻያ ሪፎርምም ዓላማዎችና ግቦችን ተቀርጾለት እና በተለያዩ ፕሮጀክቶች በማደራጀት የማሻሻያው ስራዎች እንዲሰሩ ተደርጓል፡፡

የወጪ አስተዳደርና ቁጥጥር ማሻሻያ ፕሮግራም የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደርን ውጤታማ ለማድረግና፣ ግልፅነትና ተጠያቂነትን ለማስፈን የተለያዩ 12 ፕሮጀክቶችን በመቅረጽ ስራ ላይ አውሏል፡፡

ፕሮጀክቶቹም የመንግሥት ፋይናንስ የህግ ማዕቀፍ ማሻሻያ፣የበጀት አስተዳደር ማሻሻያ፣ የመንግሥት ወጪ ዕቅድ ማሻሻያ፣ የጥሬ ገንዘብ አስተዳደርና ክፍያ አሠራር ማሻሻያ፣ የመንግሥት ሂሣብ ማሻሻያ፣ የውስጥ ኦዲት ማሻሻያ፣ የተቀናጀ የፋይናንስ መረጃ ሥርዓት ማሻሻያ፣ የመንግሥት ግዥ ሥርዓት ማሻሻያ፣ የመንግሥት ንብረት አስተዳደር ማሻሻያ፣ የሂሣብና ኦዲት ሙያ ማሻሻያ፣ የፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት እና የውጪ ኦዲት ማሻሻያ ሲሆኑ ከእነዚህ የማሻሻያ ፕሮጀክቶች መካከል የመጀመሪያዎቹ አስራ አንዱ በማሻሻያ ፕሮግራሙ የቅርብ ክትትል የሚደረግባቸው ሲሆን፣ ያስገኙት ውጤቶች በሚቀጥለው ምዕራፍ በዝርዝር ቀርቧል፡፡

የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ቀልጣፋና ውጤታማ በሆነ መንገድ ለመምራት ሁለት አዋጆች የወጡ ሲሆን እነሱም የፌዴራል መንግሥት የፋይናንስ አስተዳደር እና የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር አዋጆች ናቸው፡፡ እነዚህን አዋጆች ተከትለው የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ደንብ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ጸድቋል፡፡ አዋጆቹንና የፋይናንስ ደንቡን ለማስፈጸምና የበለጠ ለማብራራት ብዛታቸው 16 ያህል የመንግሥት የፋይናንስ፣ ግዥና ንብረት አስተዳደር መመሪያዎች ወጥተዋል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ በአዋጆቹ፣ ደንብ እና የአፈፃፀም መመሪያዎች የተገለጹትን ዋና ዋና ተግባራትን ሂደትና ዝርዝር አፈጻጸም የሚያመለክት እና ሠራተኞችን/ፈጻሚዎችን ቅልጥፍና እንዲጨምር ሊያግዝ የሚችል የአሠራር ማንዋሎች ተዘጋጅቷል፡፡

እነዚህም ማንዋሎች የፕሮግራም በጀት፣ የጥሬ ገንዘብ አስተዳደርና የክፍያ አሠራር፣ የሂሣብ አያያዝ ሥርዓት፣ የውስጥ ኦዲት፣ የክዋኔ ኦዲት፣ የመንግሥት ግዥ አፈፃፀም፣ የመንግሥት ቋሚ ንብረት አስተዳደር፣ የስቶክ ማኔጅመንና የፋይናንስ ግልጽነትና ተጠያቂነት ያጠቃልላል፡፡ ይህም የአገራችን የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር በተሟላ የህግ ማዕቀፍና ተቋማዊ አሰራር እንዲመራ አስችሏል፡፡

የመንግስት ገቢን ለማሻሻል በርካታ የማሻሻያ ተግባሮች የተከናውነው ሲሆን ዋና ዋናዎቹ፡-

  • የታክስ ፖሊሲውንና አስተዳደሩን ለማሻሻል በርካታ ጥናቶችንና ግምገማዎችን ተደርገው የገቢ ግብር፣ የታክስ አስተዳደር፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ፣ የኤክሣይስ ታክስ፣ የተርን ኦቨር ታክስ እና የኢንቨስትመንት ማበረታቻ አዋጆችንና ደንቦች ተዘጋጅተውና በየጊዜው ተሻሽለው ተግባራዊ ተደርገዋል፣
  • ለታክስ ፖሊሲው እና የመንግስትንና የግል ዘርፉን አጋርነት የሚመሩና የሚያስፈፅሙ የስራ ክፍሎች ተደራጅተው ወደስራ ተገብቷል፣
  • የመንግስትንና የግል ዘርፍ አጋርነት የፖሊሲ ሠነድ ተዘጋጅቶና አዋጅ ወጥቷል፣

በወጪ ዕቅድ ፕሮጀክት ስር የመንግሥት ኢንቨስትመንትና የመንግሥት ወጪ ፕሮግራሞች የነበሩ ሲሆን ዓላማውም በፖሊሲዎች፣ በዕቅድና በበጀት መካከል ሊኖር የሚገባውን ቅንጅት ለማሻሻል የተቀረጸ ነበር፡፡ በዚሁ መሰረትም የወጪ ዕቅድን ለማሻሻል በተሰሩ ሥራዎች የሚከተሉት ዋና ዋና ውጤቶች ተገኝተዋል፡-

  • የመንግሥት ኢንቨስትመንት ፕሮግራም ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ከዓመታዊ በጀት ጋር በማቀናጀት የመካከለኛ ዘመን ዕቅድ ለማዘጋጀት ተችሏል፤ የኢንቨስትመንት ፕሮግራሞች ቅደም ተከተል እንዲይዙ ተደርጓል፣ ለዓመታዊ የካፒታል በጀት ዝግጅት መሠረት በመሆን አገልግሏል፣
  • የመንግሥት ወጪ ዕቅድ ማሻሻያ ስራዎች ተከናውነው የመንግሥት ወጪ ፕሮግራም ማለትም የካፒታልና የመደበኛ ወጪ ዕቅድ በአንድ ላይ እንዲዘጋጅ ተደርጓል፣
  • የፌዴራል መንግሥት ኢንቨስትመንት ፕሮግራም (PIP) በየዓመቱ ለአምስት ተከታታይ ዓመታት (1991-93፣ 1992-94፣ 1993-95፣ 1994-96፣ 1995-97) ሰነዶች ተዘጋጅተው ስራ ላይ ውለዋል፣
  • በማክሮ ኢኮኖሚ እና ፊስካል ማዕቀፍ የሦስት ዓመት ተንከባላይ የገቢና ወጪ ዕቅድ በማዘጋጀት ዓመታዊ በጀት ዝግጅት በመካከለኛ ዘመን ዕቅድ ላይ የተመሰረተ እንዲሆን
  • የDebt Portfolio Analysis የጠፉ ብድሮች እና ስጋትን በማካተት በየዓመቱ ተዘጋጅቷል፣ የመካከለኛ ዘመን የብድር ስትራቴጂ (2005-2009) ተቀርጾ በስራ ላይ ውሏል፤ ከሁለተኛው ምዕራፍ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ጋር ለማቀናጀት እንዲቻል ክለሳ ተካሂዶ ተግባራዊ ተደርጓል፣
  • የዕዳ ጫና ትንተና (Debt Sustainability Analysis) ሰነድ ተዘጋጅቶ የብድር አስተዳደር ስርዓቱ በስትራቴጂ እንዲመራ ተደርጓል፣
  • የአገሪቱ የብድር አስተዳዳር ሁኔታ ግምገማ /Debt Management Performance Asse- ment/ ተከናውኗል፣
  • በየሩብ ዓመቱ የPublic Sector Debt Statiscal Bulletin ተዘጋጅቷል፣
  • የአገሪቱ የብድር መረጃ የሚመዘግቡበት ስርዓት ከነበረበት DMFAS 5.3 ወደ DMFAS 6 እንዲሻሻል ተደርጓል፣
  • ለመንግስት ባለበጀት መስሪያ ቤቶችና የልማት ድርጅቶች በመልሶ ማበደር የተላለፉ የብድር መረጃዎች ተሟልተው እንዲያዙ ተደርጓል፣

መንግስት የሂሳብ አያያዝ የማሻሻያ የተገኙ ዋና ዋና ውጤቶች፡-

  • የመንግስት ሂሳብ ቀድሞ ከነበረበት የነጠላ ሂሳብ ምዝገባ ወደ ጣምራ ሂሳብ ምዝገባ በመቀየሩ ለመንግስት ፖሊሲ ውሳኔ አመቺ የሆነ የፋይናንስ መረጃ ማቅረብ ተችሏል፣
  • የመንግስት መስሪያ ቤቶች ሂሳባቸውን ዘግተው የሚያስመረምሩበትና የሚጠየቁበት የ"Self Accounting and Reporting" ሥርዓት ተዘርግቶ ተግባራዊ ሆኗል፣
  • የመንግስት ሂሳብ አወቃቀር /Chart of Account/ የዓለም አቀፍ ደረጃ (GFS-2001) ጠብቆ እንዲሰራ አደርጓል፣
  • የመንግስት ሂሳብ አያያዝ በመረጃ ስርዓት እንዲደገፍ ተደርጓል፣
  • ከ4-5 ዓመታት ያህል ሳይዘጋና ሳይመረመር ወደ ኋላ ቀርቶ የነበረው የመንግስት ሂሳብ በየበጀት ዓመቱ እንዲዘጋ በማድረግ መመርመር ተችሏል፣
  • የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር የፑል አሰራር ስርዓት በወረዳዎች ተተግብሯል፣

በመንግሥት ግዥ እና ንብረት ማሻሻያ የተገኙ ዋና ዋና ውጤቶች፡-

  • የግዥ መደበኛ የጨረታ ሰነዶች (SBD) ተዘጋጅተው በፌዴራልና በክልሎች በሥራ ላይ እንዲውሉ ተደርጓል፣
  • የመንግሥት የግዥ ሥርዓት ባልተማከለ እና በተማከለ መንገድ እንዲመራ ተደርጓል፣
  • በመንግሥት ግዥ አፈፃፀም እና ንብረት ማስወገድ ሂደት ከተጫራቾች/አቅራቢዎች የሚቀርብ አቤቱታን አጣሪና ውሳኔ ሰጪ ቦርድ ተቋቁሟል፣
  • የአቅራቢዎች ምዝገባ በመረጃ መረብ (web based) እንዲሆን ተደርጓል፣
  • ከ220 በላይ ለሚደርሱ ዕቃዎች አገር አቀፍ ስታንዳርድ የማውጣትና የተዘጋጀውን ስታንዳርድ በሁሉም የፌዴራል መንግሥት መ/ቤቶች እንዲተገበር ተሰራጭቷል፣
  • የመንግሥት ግዥና ንብረት አስተዳደር ፕሮፌሽናል ሰርቲፊኬሽን ሥልጠና በሶስት ደረጃዎች (Basic, Essential and Advanced levels) በመሰጠት ላይ ይገኛል፣
  • በፌደራል መንግስት መ/ቤቶች የግዥ ኦዲት እየተደረገ ይገኛል፣

በውስጥ ኦዲት መሻሻያ የተገኙ ዋና ዋና ውጤቶች፡-

  • በአገር አቀፍ ደረጃ የውስጥ ኦዲት ከቅድመ-ኦዲት ወደ ድህረ-ኦዲት ስርዓት እንዲሸጋገር ተደርጓል፣ለዚሁም አፈፃፀም አደረጃጀት ተዘጋጅቶ ተግባራዊ ተደርጎል፣
  • የውስጥ ኦዲተሮች የሙያ ሥነ ምግባርና ደረጃዎች ያካተተ የውስጥ ኦዲት መመሪያ ወጥቶ በሥራ ላይ እንዲውል ተደርጎል፣
  • የወረዳ ኦዲት ኮሚቴ መመሪያ በማዘጋጀት ከ400 በላይ በሆኑ ወረዳዎች ኮሚቴው እንዲቋቋም ተደርጎ የኦዲት ክትትል ስራዎች እንዲጠናከሩ ተደርጓል፣
  • የውስጥ ኦዲተሮች ነፃ እና ገለልተኛ ሆነው ስራዎቻቸውን በጥራት እንዲያከናውኑ ለማስቻል በፌደራል ደረጃ አስተዳደራዊ ተጠሪነታቸው ለገንዘብና ኢኮኖሚ ትብብር ሚኒስቴር ተደርጓል፡፡

እና የግሉ ዘርፍ ለኢኮኖሚ ዕድገት ያላቸውን ወሳኝነት የማበላለጥ ወይም ለአንዱ ቅድሚያ የመስጠት አዝማሚያዎች የተከሰቱ ቢሆንም በአጭር ጊዜ ከድህነት ተላቀው ብልፅግናን የተላበሱ አገሮች ተሞክሮ የሚያሳየው የመንግሥትን ሚና ወሳኝ መሆኑን ነው፡፡ በመሰረቱ ማንኛውም ለልማት የቆመ መንግስት ሁሉ ልማታዊ መንግስት ነው ማለት ይቻላል፡፡ ሆኖም በኢኮኖሚ ልማት ንድፈ ሃሳብ ልማታዊ መንግስት በመባል የሚታወቁት የምስራቅ ኤሽያ አገሮች በተለይም የኮሪያና የታይዋን መንግስታት ዓይነት የልማት አቅጣጫ የሚከተሉት ሲሆኑ፣ ይህ የልማታዊ መንግስት ኢኮኖሚ ሞዴል እነዚህ አገራትን በአጭር ጊዜ ውስጥ ከድህነት ተላቀው በኢኮኖሚያቸው የበለጸጉ አገራትን እንዲቀላቀሉ አስችሏቸዋል፡፡ ለዚህ ውጤት ደግሞ መንግስታት በኢኮኖሚው እንቅስቃሴ ውስጥ የነበራቸው ሚና የጎላ ነበር፡፡ በአጠቃላይ ሲታይ ልማታዊ መንግስታት በ ዋና ባህሪት ከሌሎቹ ይለያሉ፡፡ እነዚህም በመጀመሪያ ልማትን የህልውናቸው ጥያቄ ያደረጉ መንግስታት በመሆናቸው ከድህነት ለመውጣት ብርቱ ትግል ያደርጋሉ፤ በሁለተኛነት መንግስት ባለሃብቱን በሙሉ ልብ የመደገፉ መርህ እንደተጠበቀ ሆኖ ከባለሃብቱ ፖለቲካና አስተሳሰብ ተጽዕኖ ነፃ በመሆን የሚንቀሳቀስ ሲሆን፣ በሶስተኝነት ደግሞ ልማታዊ መንገዱ ለተከታታይ ዓመታት ቀጣነት እንዲኖረው ልማታዊነት የአስተሳሰብ የበላይነቱን ያረጋገጠበት ሥርዓት እንዲሆን ያደርጋሉ፡፡

በአገራችንም ከላይ የተዘረዘሩትን ሦስት የልማታዊ መንግስት ባህሪያት በመያዝ እና በተጨማሪም በአራተኛነት ዲሞክራሲን በአገሪቱ ማስፈን የሞት ሽረት ጉዳይ አድርጎ በመውሰድ እንዲሁም በአምስተኛነት የህዝብ ተሳትፎና ባለቤትነትን የልማታዊ መንግስቱ ባህሪያት አድርጎ በመውሰድ መንግስት የልማታዊ መንግስት ኢኮኖሚ ሞዴል መከተል ከድህነትና ከኋላ ቀርነት በማላቀቅ አገሪቱን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ መካከለኛ እና በሂደትም ወደ በለፀገ ኢኮኖሚ ሊያሸጋግር እንደሚችል በመረዳት ከአገሪቱ ተጨባጭ ሁኔታ አንጻር ስርዓቱን በተለይ ከ1994 ዓ.ም. ጀምሮ በመተግበር ላይ ይገኛል፡፡ በልማታዊ መንግስት ስርዓት መንግስት በኢኮኖሚው ውስጥ ያለው ሚና ከፍተኛ በመሆኑ፣ በመንግስት በኩል ከፍተኛ የሆነ ሀብት ወጪ ተድርጎ ኢኮኖሚውን የማንቀሳቀስ፣ የገበያ ክፍተት ባለበት ክፍተቱን የመሸፈን ተግባር ይከናወናል፡፡ ይህም ውሱን የሆነውን የመንግስት ሀብት በቁጠባና በብቃት ማስተዳደርና ጥቅም ላይ ማዋልን የሚጠይቅ ይሆናል፡፡ ለዚህም የመንግስትንም ሆነ የግሉን ዘርፍ የማስፈጸም አቅም መገንባት እና የፋይናንስ አቅም በከፍተኛ ደረጃ ማሳደግን ይጠይቃል፡፡ ለዚህም ባለፉት ተከታታይ 15 ዓመታት ድህነት ተኮር ለሆኑት የመሰረታዊ አገልግሎቶችና እና የመሰረተ ልማት ፕሮግራሞች መንግስት ከፍተኛ በጀት በመመደብ፣ የገበያ ክፍተት ባለበት ላይ በቀጥታ ጣልቃ በመግባት፣ የግሉን ዘርፍ ለማበረታታት የሙያ ድጋፍ በመስጠት፣ ብድር በማመቻቸት፣ የግብር እፎይታን ጨምሮ ለሚያካሂዷቸው ኢንቨስትመንቶች የቀረጥ ነፃ መብት ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማድረግ ዘርፍን የመደገፍ ስራ ተሰርቷል፡፡

ለዚህም በአገራችን በተለይ ባለፉት 15 ዓመታት በሁሉም ዘርፍ መጠነ ሰፊ የአቅም ግንባታ ማሻሻያ ፕሮግራሞች ተነድፈው በመተግበራቸው የአገሪቱ የማስፈጸም አቅም በከፍተኛ ደረጃ

ተሻሽሏል፡፡ ለዚህም በተለይ በትምህርት፣ በጤና፣ በመንገድና በመጠጥ ውሃ ተደራሽነትና ሽፋን፤ በኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት፣ በግብርና ምርት ዕድገት፣ በኢንዲስትሪ መስፋፋት ወዘተ የተገኙት ዕድገቶች በአመዛኙ መንግስት በቅድሚያ ተነሳሽነት ያከናወናቸው ናቸው፡፡ ይህም በመሆኑ ባለፉት ተከታታይ አስር ዓመታት የአገሪቱ ኢኮኖሚ ከአስር በመቶ በላይ በማደግ ከዓለም ቀዳሚ የኢኮኖሚ ዕድገት ከተመዘገበባቸው ጥቂት አገራት አንዷ ለመሆን ከመብቃታችን በተጨማሪ የህዝባችን የድህነት ምጣኔ ከግማሽ በላይ ቀንሷል፡፡

የመንግስት ፋይናንስ አስተዳደር ሥርዓቱን በማሻሻል የማስፈጸም አቅሙን ለመገንባት በተሰሩ ስራዎችም በፌዴራልና በብሄራዊ መንግስታት እስከ ታችኛው የአስተዳደር እርከን ድረስ መጠነ ሰፊ የፋይናንስ ህግና የአሰራር ስርዓት ማሻሻዎች የተደረጉ ሲሆን፣ በዚህም የመንግስት ወጪ አስተዳደሩ በዘመናዊና ቀልጣፋ ከመሆኑም በተጨማሪ የመንግስት ገቢን በከፍተኛ መጠን ሊያድግ ችሏል፡፡ በተለይም ከ1994 በፊት በተካሄዱ የመንግሥት ገቢ ማሻሻያ እርምጃዎች የወራሽነት ባህሪ የነበራቸውን የታክስ ማስከፈያ መጣኔዎች ዝቅ በማድረግ፣ የታክስ መሠረቱን በማስፋትና አስተዳደሩን በማሻሻል እንዲሁም ያልተማከለ የመንግሥት ፋይናንስ አስተዳደር ዕውን በማድረግ የሀገር ውስጥ ገቢን ለማጐልበት ጥረት ተደርጓል፡፡ ሆኖም የተወሰዱት እርምጃዎች የሚፈለገውን የፋይናንስ አቅም ማመንጨት ባለመቻላቸው ተጨማሪና የተጠናከሩ የገቢ ፖሊሲና አስተዳደራዊ ማሻሻያዎችን ማድረግ ግዴታ ሆኗል፡፡

ታክስ የመንግሥት ዋናው የገቢ ምንጭ በመሆኑ ለውጤታማነቱ መሥራት ግዴታ ነው፡፡ የታክስ ፖሊሲው ተፈላጊውን ገቢ ከማመንጨት ባሻገር ሌሎች ዓላማዎችን ለማስፈፀም መዋል ይኖርበታል፡፡ መንግሥት የታክስ ፖሊሲው የዜጐችን የመሥራት ፍላጐት ለማበረታታት፣ የገቢ ልዩነት ለማጥበብ፣ የኢንቨስትመንትን አቅጣጫ ለመምራት፣ እንዲሁም ያልተፈለጉ ምርትና አገልግሎቶችን ለመቆጣጠር ይገለገልበታል፡፡ በአገራችንም ሥራ ላይ የዋሉ የታክስ ፖሊሲዎች በዋናነት ገቢን ለማሳደግ ትኩረት ያደረጉ ቢሆንም እነዚህን ተጓዳኝ የፖሊሲ መሣሪያዎች ተግባራዊ ለማድረግ ረድተዋል፡፡ በሌላም በኩል የታክስ ፖሊሲው የታክስ አስተዳደሩ ውጤታማ፣ የማያዳላና አስተዳደራዊ ብቃትን የሚያጐለብት እንዲሆን የማድረግ ሥራ ተከናውኗል፡፡ እነዚህንም የታክስ ፖሊሲ ዓላማና መርሆዎች ተግባራዊ ለማድረግ የተከናወኑ የታክስ ፖሊሲ ማሻሻያ እርምጃዎች የሚከተሉትን መሠረት ያደረጉ ናቸው፡፡ እነዚህም፡-

  • በወጪ ንግድ ላይ ጥገኛ የሆነውን ገቢ በአገር ውስጥ የፍጆታ ታክሶች ላይ እንዲመሠረት ማድረግ፣
  • የታክስ ጫናውን ከምርት ይበልጥ በፍጆታ ላይ ማሸጋገር፣
  • የታክስ ጫናውን ከድሀው የህብረተሰብ ክፍል ይልቅ የተሻለ ገቢ ያለው እንዲሸከም ማድረግ፣

ባለፉት በርካታ ዓመታት ሥራ ላይ የዋለው የፊሲካል ፖሊሲ የመንግሥት ገቢ ለማሳደግ ትኩረት ከመሰጠቱም ባሻገር የተሰበሰበው ገቢ የመንግሥትን ኃላፊነት ለመወጣት በሚያስችሉ ልማትን ለማፋጠንና፣ ድህነትን ለመቀነስና መሠረታዊ አገልግሎቶችን ለማቅረብ በሚረዱ የወጪ ዘርፎች የተመደበና አስተዳደሩም ውጤታማ እንዲሆን በርካታ የማሻሻያ እርምጃዎች ተቀርጸው ተግባራዊ ሆነዋል፡፡

ከ1984-1993 በነበሩት 10 ዓመታት የሽግግሩ ወቅት መንግሥት ሆነ የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ መንግሥት አገሪቱን ከድህነት ለማውጣት የሚያስችል መሠታዊ የኢኮኖሚ ማሻሻያ ፕሮግራሞች ተነድፈዋል፡፡ ፕሮግራሞቹን ተግባራዊ ለማድረግ የሚያስችሉ እስትራቴጂዎችና ስልቶች የተዘረጉ ሲሆን ዋና ዋና የኢኮኖሚና ማህበራዊ ክፍላተ ኢኮኖሚዎች የሚመሩበት ፕሮግራሞችንም ሥራ ላይ ውለዋል፡፡ ሆኖም እነዚህ እንቅስቃሴዎች ፈጣንና ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚና ማህበራዊ ለውጦችን ማምጣት ባለመቻላቸው መንግስት በ ዓ.ም ወዲህ የኢኮኖሚ ፖሊሲውን በማሻሻልከድህነት በአጭር ጊዜ ለመላቀቅና የኢኮኖሚ ልማትን ለማፋጠን የልማታዊ መንግስት ሞዴል ተመራጭ ሆኗል፡፡የኢኮኖሚ ፖሊሲን ከልማታዊ መንግስት ሞዴል ጋር በማጣጣም ልዩ ልዩ የክፍላተ ኢኮኖሚ ፖሊሲ፣ እስትራቴጂና ስልቶችን በመንደፍ ተግባራዊ ሆነዋል፡፡ ከእነዚህ መካከል ሚከተሉት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ እነዚህም፡-

  • የገጠር ልማት ፖሊሲ፣ እስትራቴጂ እና ስልቶች፣
  • የኢንዱስትሪ ልማት እስትራቴጂ፣
  • የማስፈፀም አቅም ግንባታ እስትራቴጂና
  • በኢትዮጵያ የዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ናቸው፡፡

በእነዚህ የመንግሥት ፖሊሲ፣ እስትራቴጂና ፕሮግራሞች ላይ መሠረታዊ ጽሁፎች እንዲዘጋጁ፣ ለዜጐች እንዲሠራጩና በውይይት እንዲዳብሩ ተደርጓል፡፡ ይህም አካሄድ በአገሪቱ የልማት እስትራቴጂ ስልትና አፈጻጸም ላይ አስፈጻሚ አካላትና ህዝቡ በቂ ዕውቀትና ግንዛቤ እንዲኖራቸው እንዲሁም አገራዊ የጋራ አመለካከትና እምነት እንዲኖር ለማድረግ ረድቷል፡፡ እነዚህን መሠረታዊ የመንግሥት ፖሊሲና እስትራቴጂዎች መሠረት በማድረግ ከ1995 ጀምሮ ተከታታይነት ያላቸው የድህነት ቅነሳ ፕሮግራሞች ሥራ ላይ ውለዋል፡፡ የመጀመሪያው የዘላቂ ልማትና የድህነት ቅነሳ ፕሮግራም (SDPRP) ከ1995-1997 ተግባራዊ የተደረገ ሲሆን፣ በቀጣይም በዚህ ፕሮግራም የአፈጻጸም ግምገማ ላይ በመንተራስ ከ1998-2002 የቆየ ሁለተኛው ፈጣንና

ቀጣይነት ያለው ልማት በማስፈን ድህነትን በሂደት ማስወገድ ዓላማው ያደረገ (PASDEP) የልማት ዕቅድ ተዘጋጅቷል፡፡ በአሁኑ ወቅት በመተግበር ላይ ያሉት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች፤ (GTP) ከ2003-2007፣ እንዲሁም (GTP) IIከ2008-2012 በመካሄድ ላይ ይካሄዳል፡፡

የተጠቀሱት የልማትና ድህነት ቅነሣ ብሎም አገሪቱን ከድህነት ለማላቀቅ እንደሚረዱ የታመነባቸው ፕሮግራሞች ከቀበሌ እስከ አገር አቀፍህ ህብረተሰቡን እንዲሁም የአገሪቱን የልማት አጋሮች በማሳተፍ የተዘጋጁ ናቸው፡፡ እያንዳንዱ የልማት ዕቅድም አገራዊና ዓለም አቀፍ ነባራዊ ሁኔታዎችን እንዲሁም ወቅታዊ የአገሪቱን ሁኔታ በማገናዘብ የየራሳቸውን መሠረታዊ የትኩረት አቅጣጫዎች ያስቀምጣሉ፡፡ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች ፈጣን ዕድገትን ከማስገኘት ባሻገር በሁሉም ዘርፎች የተሻለ ውጤትን በማስመዝገብ አገሪቱን ከድህነት በማላቀቅ በሚቀጥሉት 10-15 ዓመታት ወደ መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገሮች ለማሰለፍ የሚያስችሉ የኢኮኖሚና ማህበራዊ ዕድገት መሠረቶችን ለመገንባት ዓላማ ያደረጉ የልማት ምሶሶዎችን ቀምሯል፡፡ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በሚል ርዕስ የተዘጋጀው የ5 ዓመቱ የልማት ዕቅድ ዓበይት ዓላማዎች የሚከተሉት ናቸው፡፡ እነዚህም፡-

  • ቢያንስ 11 በመቶ ዓመታዊ አማካይ የአጠቃላይ ምርት ዕድገት በማስመዝገብ የምዕተ ዓመቱን የልማት ግቦች ማሳካት፣
  • የትምህርትና ጤና አገልግሎቶችን ተደራሽነትና ጥራት በማረጋገጥ የማህበራዊ ዘርፉን የምዕተ ዓመቱን ግቦች ማሳካት፣
  • የተረጋጋ ዲሞክራሲያዊና ልማታዊ መንግሥት በመፍጠር ለዘላቂ አገራዊ ልማት አመች ሁኔታ መፍጠር፣ እና
  • በተረጋጋ የማክሮኢኮኖሚ ማዕቀፍ ከፍ ብለው የተጠቀሱትን ዓላማዎች በማሳካት ቀጣይነት ያለው የኢኮኖሚ ዕድገትን ማረጋገጥ የሚሉት ናቸው፡፡

እነዚህን ዓላማዎች በማሳካት ፈጣን፣ ቀጣይና ሁሉን አቀፍ የሆነ የኢኮኖሚ ዕድገት ለማምጣት የሚያስችሉ እስትራቴጂዎች በዕቅዱ ተካተዋል፡፡ የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድም ሆነ ያለፉት የዘላቂ ልማትና ድህነት ቅነሣ ፕሮግራሞች አመርቂ ውጤት ማሳየታቸውን በየጊዜው የተደረጉ የአፈጻጸም ግምገማዎችና ሪፓርቶች አሳይተዋል፡፡

አገራችን ዘርፈ ብዙ የልማት እንቅስቃሴ በማድረግ የዜጐችን የኢኮኖሚና ማህበራዊ ህይወት ለማሻሻል በድህነት ላይ ጦርነት መክፈቷ ይታወቃል፡፡ ለዚህ ዓላማ መሳካትም መንግሥት አግባብ ያለው ፖሊሲን ከመቅረፅና ለግሉ ክፍለ ኢኮኖሚ አመች ሁኔታን ከመፍጠር ባሻገር ድህነት ተኮር